አዲስ ነገር – የአፍሪካ የፋሽን ሳምንት

ከ30 ሃገራት የተወጣጡ ዓለም አቀፍ አምራችና ላኪዎች ምርቶቻቸውን በአለም ዙሪያ የሚያስተዋውቁበት 8ተኛው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አስታወቀ።መድረኩ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ማህበር ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ጋር በመተባበር ያዘጋጀው እንደሆነና ከጥቅምት 25 እስከ 28 እንደሚቆይም ተገልጿል።ከ200 በላይ ዓለም አቀፍና የሃገር ውስጥ አምራችና ላኪዎች እንደሚሳተፉና ምርቶቻቸውንም በአለም ዙሪያ ለሚገኙ ከ6ሺህ ለሚበልጡ የንግድ ባለሞያዎችና ግብዓት አቅራቢዎች እንደሚያስተዋውቁ ተነግሯል።ይህ መድረክ ትኩረቱ የአፍሪካ ምርቶች ላይ ነው የተባለ ሲሆን ለአፍሪካውያን አምራቾችም የንግድ ትስስር የሚፈጥር ይሆናል ተብሏል።በመድረኩ ላይ በአልባሳት ምርት የተሰማሩ የአፍሪካ ሃገራት የጨርቃጨርቅ፣ የአልባሳት፣ የቴክኖሎጂ፣ የቆዳ ውጤቶችንና የፋሽን ዲዛይኖችን ይዘው እንደሚቀርቡና በእለቱ የፋሽን ትርኢትና ኮንፍረንስ እንደሚኖርም ተነግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New