News

አዲስ ነገር – የውጭ ምንዛሬ ጫና

ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ጫና ውስጥ የወደቀችው ባለፉት 2 አመታት ከልማት አጋሮች ይገኝ የነበረው የድጋፍ መጠን የተጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ እንደሆነ ተነገረ፡፡የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከብሔራዊ የቴሌቭዢን ጣቢያ ኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳመለከቱት በእነዚህ አመታት የነበረው የድጋፍ መጠን በመቀነሱ እንዲሁም የአለም አቀፍ እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ ሳቢያ ለውጪ የሚከፈለው የክፍያ መጠን ደረጃ በማደጉ የውጪ ምንዛሬ ጫና ውስጥ መገባቱን አመልክተዋል፡፡በመሆኑም የውጪ ምንዛሬ ግኝትን የሚያሳድጉ ስራዎች ላይ መስራት ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው አቅጣጫ ከሰጠባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛ መሆኑን በማንሳት ከፍተኛ የሆነ የተከማቸ እዳ መኖሩንና እሱም መከፈል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡በተጨማሪም የነዳጅ እና ማዳበሪያ አቅርቦት በአስተማማኝ ደረጃ እንዲቀርብ እና መሰረታዊ ሸቀጦች በኢኮኖሚው ውስጥ ሁሌም እንዲገኙ እየሰራ እንደሆነና ኤክስፖርትን በማሳደግ ደረጃም ጥሩ ውጤት እየመጣ መሆኑን ሚኒስትሩ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New