News

አዲስ ነገር – አዲስ በረራ ወደ ዙሪክ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ አዲስ በረራ ልጀምር ነው ብሏል፡፡

በረራው በሳምንት 3 ቀናት የሚደረግ ሲሆን በያዝነው የፈረንጆቹ ኦክቶበር ወር መጨረሻ የመጀመሪያ በረራውን እንደሚያደርግ አመልክቷል።ይህም አየር መንገዱ ወደ ጄኔቫ የሚያደርገውን የቀደመ በረራ ጨምሮ በስዊዘርላንድ ያለውን መዳረሻ ወደ ሁለት እንዲሁም በአውሮፓ አህጉር ያለውን አጠቃላይ መዳረሻ ደግሞ ወደ 19 ያሳድገዋል ተብሏል።በተጨማሪም አየር መንገዱ ቀደም ሲል ወደ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ በሳምንት ለ3 ቀናት ያደርግ የነበረውን በረራ ከያዘነው የፈረንጆቹ ወር መጨረሻ ጀምሮ በሳምንት ወደ አራት ቀናት አሳድጋለሁ ብሏል።በተያያዘም አየር መንገዱ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው አራተኛው የአፍሪካ አቪዬተር ታወር አዋርድ በ2022 በሶስት የተለያዩ ዘርፎች ተሸላሚ መሆኑን ገልጾ የቦርድ ሰብሳቢው ግርማ ዋቄም የአፍሪካ አቪዬተር ሆል ኦፍ ፌም 2022 አሸናፊ መሆናቸውን ተናግሯል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New