News

አዲስ ነገር – የሰላም ስምምነቱ

በትናንትናው እለት በመንግስትና በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት በተፈረጀው ህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መልዕክት አስተላልፈዋል።በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር አብይ በመልዕክታቸው ስምምነቱ ኢትዮጵያ ያቀረበችው ሀሳብ መቶ በመቶ ተቀባይነት ያገኘበት ነው በማለት ተናግረዋል።በአንድ ሀገር ወስጥ ከአንድ መከላከያ በላይ አያስፈልግም በሚለው ጉዳይ ላይ ከስምምነት መደረሱንም የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በትግራይ ክልል ህገወጥ በሆነ መንገድ የተደረገው ምርጫ በህጋዊ ምርጫ መተካት አለበት የሚለውም ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጸዋል።የአንዳንድ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አከራካሪ ቦታዎችም ጉዳይ የሰው ህይወት ሳይጠፋ በድርድርና በሀገሪቱ ህግ መሰረት ምላሽ እንዲያገኝ መተማመን ላይ መደረሱንም ተናግረዋል።አሁንም ለሰላም ላባችንን ብናፈስስ፣ በጦርነት የወደሙብንን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት ካለን ላይ ብናዋጣ እናተርፋለን እንጂ አንጎዳምም ብለዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New