News

አዲስ ነገር – ትራቨል ፖርት እና አየር መንገዳችን

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትራቭል ፖርት ከተሰኘው የጉዞ ቲኬት አመቻች ድርጅት ጋር የነበረውን የስራ ውል ለተጨማሪ 5 አመታት ማራዘሙን አስታውቋል፡፡የስምምነቱ መታደስ የአየር መንገዱን አገልግሎቶች በስፋት ከማስተዋወቅ ባሻገር ቀልጣፋ የደንበኞች ግልጋሎትንም የሚያስቀጥል ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ላለፉት 25 አመታት ከትራቭል ፖርት ጋር ሲሰራ የቆየው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የጉዞ ኤጀንሲዎች ትራቭል ፖርትን በመጠቀም አገልግሎት እንዲሰጡ ሲያደርግ መቆየቱን ያሳወቀ ሲሆን በዚህም መሰረት አሰራሩን ለመጠቀም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሲስተሙን በመጠቀም የትኬት ሽያጭ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን አስታውሷል።ትራቭል ፖርትም ከአየር መንገዱ ጋር የነበረውን ውል ማራዘሙን እንደ ትልቅ እድል እንደሚመለከተው ጠቅሷል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New