አዲስ ነገር – የዓለምን ትኩረት የሳበው የቱርክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ ምርጫ ሊካሄድ ነው።

የዓለምን ትኩረት በሳበው የቱርክ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊውን ለመለየት በድጋሚ ምርጫ ሊካሄድ እንደሆነ እየተዘገበ ነው።
በምርጫው እየተፎካከሩ ያሉት 4ቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ተፎካካሪዎቹ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃንና ተቀናቃኛቸው ከማል ኪሊስዳሮግሉ እስካሁን በተደረገው የድምፅ ቆጠራ አንዳቸውም ከ50 ከመቶ በላይ የመራጮች ድምፅ ማግኘት ባለመቻላቸው ከ13 ቀናት በኋላ ለሁለተኛ ዙር ምርጫ እንደሚፎካከሩ ነው የተዘገበው ።
ኤርዶሃን 49 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ፤ ተፎካካሪዎቸው ኪሊስዳሮግሉ ከ45 በመቶ በላይ ድምጽ ነው ያገኙት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድን ዋቢ ያደረገው የአር ቲ ይፋ ዘገባ፡፡
ፕሬዚዳንት ኤርዶሃን የምርጫ ቦርድ ለሁለተኛ ግዜ የማጣሪያ ምርጫ የሚያደርግ ከሆነ ለዛም ዝግጁ እንደሆኑ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል፡፡
🇸🇴#ሶማሊያ
የመንግስታቱ ድርጅት በሶማሊያ በደረሰ ከባድ የጐርፍ አደጋ 22 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አስታወቀ፡፡
የድርጅቱ የሰብዓዊ ድጋፎች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በሶማሊያ ሂራን ግዛት የሸበሌ ወንዝ ሞልቶ በተከሰተዉ የጐርፍ መጥለቅለቅ ከሞቱት 22 ሰዎች በተጨማሪ 219 ሺ ሰዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡
በጐርፍ መጥለጥለቁ በሂራን ግዛት ያለችው የቤል ዋይኔ ከተማ በእጅጉ መጐዳቷ ሲነገር አጠቃላይ በጐርፍ አደጋው የተጐዱ ሰዎች ቁጥር በትንሹ 460 ሺ ይደርሳል መባሉን ፍራንስ ቱዌንቲ ፎር ዘግቧል።
🇿🇦#ደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደቡብ አፍሪካ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ገለልተኛ አቋሟን ይዛ ትቀጥላለች አሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ደቡብ አፍሪካ ለዘመናት ስታራምድ የነበረውን ገለልተኛ ፖሊሲዋን እንድታቆም ግፊት ሲካሄድባት እንደነበር ገልፀው አሁንም በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ይሄንኑ የገለልተኛ ፖሊሲያችንን ይዘን እንቀጥላለን ብለዋል።
በደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ አምባሳደር ሩበን ብሪጌቲ ደቡብ አፍሪካ ለሩሲያ በድብቅ የጦር መሳሪያ እየረዳች ነው ማለታቸውን ተከትሎ የሲሪል ራማፎሳ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያካሂድ መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
#አፍሪካ
አፍሪካ የታዳሽ ኃይሏን ለማልማት ከ700 ቢሊዮን ዶላር በላይ የፋይናንስ ድጋፍ እንደምትፈልግ አንድ ጥናት አመለከተ።
ይህንን ያሉት የስታንዳርድ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኬኒ ፊህላ ሲሆኑ የባንካቸውን የዳሰሳ ጥናት ይፋ አድርገው አፍሪካ ከዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ድጋፍ ትሻለች ብለዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም አፍሪካ የምትሻውን ይሄን ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ለማሟላት የአፍሪካ ባንኮች አቅም የላቸውም ሲሉ ነው ከብሉምበርግ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ያብራሩት፡፡
በአፍሪካ 600 ሚሊዮን ሕዝብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደማያገኝ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ አር ቲ ዘግቧል፡፡

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New