አዲስ ነገር – የዓለም ባንክ ድጋፍ

የዓለም ባንክ በሴቶች፣ ህጻናትና በማህበራዊ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራትን መደገፉን እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
ባንኩ ይህን ያስታወቀው በኢትዮጵያ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶችን ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ባካሄደው ውይይት ላይ ሲሆን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ዘርፍ እያከናወነ የሚገኘውን ተግባራት ከአስር ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ጨምሮ ገለጻ አድርጓል፡፡
በዚህም ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር የሚከናወኑ ስራዎች በዋናነት የከተማና የገጠር ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የሴፍት ኔት ፕሮግራም፣ ቀውስን የመቋቋምና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ፕሮጀክት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ብሄራዊ የስርአተ ጾታ ፖሊሲና የስርአተ ጸታ እኩልነት ፍኖተ ካርታ፣ እንዲሁም ተቋማን የማጠናከርና ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃትን በተመለከተ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በውይይቱም በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል ለማከናወን ስለታሰቡ ስራዎች ተገልጾ በዋናነት የአረጋዊያን ማእከል ግንባታ፣ የማህበራዊ ጥበቃ ስራን ለማዘመን የሚያስችል የዲጂታል ስርአትን ለመገንባት እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል የዓለም ባንክ ድጋፉን አጠናክሮ እዲቀጥል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጠይቀዋል፡፡
የዓለም ባንክ የዘለቄታዊ ማህበራዊ ዘርፍ ግሎባል ዳይሬክተር የሆኑት ሎውሲ ኮርድ በበኩላቸው ባንኩ በኢትዮጵያ ድጋፉን በተለያዩ ምዘርፎች ላይ እንደሚያደርግና ወደፊትም በጋራ የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት እገዛ እንደሚያደርግ ማስታወቁን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገጽ ገልጿል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New