News

አዲስ ነገር – የውጭ ጉዳይ ሪፖርት

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኤርትራ ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሰረት በማድረግ በትብብር እየሰራን እንገኛለን አሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር ለማሸጋገር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የድንበር አካባቢ ንግድና የነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የወደብ አጠቃቀም፣ የንግድ ልውውጥ፣ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽንና የመሳሰሉ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የትብብር ማዕቀፎችን ለማበጀት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የዓለም ስርዓት ተገማች ያለመሆን፤ በተለያዩ ፍላጎቶችና የአሰላለፍ ለውጦች ምክንያት የዲፕሎማሲ ፈተና የበዛ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ቢሆንም እንደተለመደው በዜጎች ትብብርና ተሳትፎ ለመቋቋም እንሰራለን ብለዋል፡፡
በጂኦ ፖለቲካ ፍላጎትና በልዩ ልዩ ውስጣዊ ሁኔታዎች ዲፕሎማሲው ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ቀድሞ መንቀሳቀስ የሚፈለግበት ዘመን ላይ መድረሱንም ጠቁመዋል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New