Sports

EBS SPORT – የኢትዮጵያ እና የግብፅ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከግብፅ ጋር የሚያደርገውን የምድብ ጨዋታ በተመለከተ የስታዲየም ምርጫውን ለካፍ አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው ማድረግ ለሚገባው የማጣሪያ ጨዋታ የካፍን መመዘኛ የሚያሟላ ስታዲየም እንደሌለ ይታወቃል፡፡ ያንን ተከትሎ የአፍሪካ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ አካል ካፍ ኢትዮጵያ ጨዋታዋን በገለልተኛ ሜዳ እንድታደርግ ዉሳኔ አሳልፏል።

ዋልያዎቹ ከግብጽ የሚኖርባቸውን የሜዳቸውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በማላዊ ለማድረግ ከዉሳኔ ላይ መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸዉንም እዚያዉ ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጫውተው ከግብጽ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New