አዲስ ነገር – የዓለም የቀን ውሎ
የብሪታንያ ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ህልፈትን ተከትሎ የአለም መሪዎች ሀዘናቸውን እየገለፁ መሆኑ ተነግሯል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የፈረንሳዩ መሪ ኢማኑኤል ማክሮን ፣ የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂ ፒንግን ጨምሮ በርካታ የአለም መሪዎች ትናንት በ96 አመታቸው ላረፉት ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን አስተላልፈዋል።የንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ እረፍት ከተሰማበት ሰአት አንስቶ እንግሊዛውያን ብርቱ ሀዘናቸውን በመግለፅ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የብሪታንያው ልኡል ቻርለስ የአገሪቱ አዲሱ ንጉስ ሆነው ተሾመዋል።ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ማረፋቸውን ተከትሎ ነው ልኡሉ ቻርለስ 3ኛ ተብለው በይፋ የብሪታንያ ንጉስ ሆነው የተሾሙት ።አዲሱ የብሪታንያ ንጉስ ቻርለስ 3ኛ የጋራ የብልፅግና አገራት መሪ ብሎም የ 15 አገራት ንጉስ ሆነው እንደሚያገለግሉ ቢቢሲ ዘግቧል።
ቱርክ የሩሲያ የእህል ምርትን ለአፍሪካ አገራት ለመላክ ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃለች።የቱርኩ ፕሬዚዳንት ታይፕ ኤርደዋን የዩክሬን እህል ለአውሮፓ መሄዱ ትክክል አለመሆኑን ገልጸው ቱርክ የሩሲያን እህል ለአፍሪካ ለመላክ ዝግጁ ነች ብለዋል።የመንግስታቱ ድርጅት ፣ ቱርክ ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን ከዩክሬን እህል ወደ አፍሪካ እንዲላኩ ከ 3 ወራት በፊት ስምምነት መድረሳቸውን አስታውሶ አናዶሉ ዘግቧል።
ቱርክ የአሸባሪውን የአይ ኤስ ኤስ ከፍተኛ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ይፋ አደረገች ።የቱርክ ፕሬዚዳንት ታይፕ ኤርዶዋን የአገሪቱ የፀጥታ ሃይሎች ባካሄዱት ዘመቻ የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ አመራር የሆነውን አቡ ዘይድን በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል ::የአይ ኤስ ኤስ አመራሩ አቡ ዘይድ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ቱርክ ገብቶ ሲንቀሳቀስ የደህንነት ሃይሎች ተከታትለው በቁጥጥር ስር አውለውታልም ሲሉ ኤርዶዋን መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::
ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ
👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)
👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00
ዘወትር ቅዳሜ
👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት
ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።
አዲስ ነገር / What’s New