አዲስ ነገር – ፈተናውን የወደቀው ፌስቡክ

ፌስቡክ በኢትዮጵያ ሶስት ብሄሮች ላይ ያተኮሩ የጥላቻ ንግግሮችን ያዘሉ ማስታወቂያዎች ተልከውለት በገጹ እንዲቀርቡ ፍቃድ በመስጠቱ ፈተናውን መውደቁ ተገለጸ፡፡
የሙከራ ማስታወቂያዎቹን የሰጡት ግሎባል ዊትነስ እና ፎክስ ግሎቭ የተባሉ ሁለት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋማት ዳግም አፈወርቅ ከተባለ ጥናት አድራጊ ጋር በመተባበር መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ምርመራው የተደረገው የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር መለያ ምን ያህል ትክክል እንደሆነ ለመፈተንና የኩባንያው የደህንነት መቆጣጠሪያዎች ሁከት የሚያባብሱ ማስታወቂያዎችን የመከላከል አቅማቸውን ለመፈተሽ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
በዚህም በአማርኛ ቋንቋ በፌስቡክ የተጻፉ 12 የከፉ የጥላቻ ንግግሮችን የለዩት ተቋማቱ እነዚህን ይዘቶች ለኩባንያው እንደ ማስታወቂያ በማቅረብ ፍቃድ የጠየቁ ሲሆን ፌስቡክ የቀረቡለትን 12ቱንም የጥላቻ ንግግሮች በማስታወቂያ መልክ በገጹ እንዲቀርቡ ፈቃድ መስጠቱን ግሎባል ዊትነስ በድረገጹ አስነብቧል፡፡
ታድያ እንደተቋሙ መረጃ ከሆነ ፌስ ቡክ ለተቀበላቸው አሉታዊ ማስታወቂያዎች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እንዲታተሙ መፍቀድ እንዳልነበረበት ያመነና ይቅርታም የጠየቀ ሲሆን ለኢትዮጵያ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የደህንነት ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ከፍተኛ ትኩረት እሰጣለሁ ማለቱን ገልጿል፡፡

የኢቢኤስ የአዲስ ነገር / What’s New መረጃዎችን በሚከተሉት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይከታተሉ::

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New