አዲስ የሚገነቡት ት/ቤቶች
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ባልተገነቡባቸው 727 ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ እንደ ሀገር ሊገነቡ ከታቀዱት 1452 ትምህርት ቤቶች መካከል ግማሽ የሚሆኑት የሚገነቡት በትምህርት ሚኒስቴር መሆኑንና ቀሪዎቹ ደግሞ በክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለሚያስገነባቸው ትምህርት ቤቶች የሚያስፈልገውን 40 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከአጋር ድርጅቶች ማግኘቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ የእነዚህ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ሲጠናቀቅ 87,120 ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
