የትራምፕ የግድያ ሙከራ ተጠርጣሪ
ባሳለፍነው ቅዳሜ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ የተጠረጠረው ግለሰብ ትላንት ፍርድ ቤት ሲቀርብ በፕሬዝዳንቱ ላይ የግድያ ሙከራ ክስ እንደቀረበበት ተሰምቷል።
የ31 ዓመቱ ተጠርጣሪ ኮል ቶማስ ሁለት የጦር መሣሪያዎችንና ሦስት የስለት መሣሪያዎችን በመያዝ የሂልተን ሆቴልን የፍተሻ ጣብያ አምልጦ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ አድርጓል የሚል ክስ ነው የቀረበበት፡፡
በዚህ ጥቃት በአንድ የፀጥታ ኃይል ላይም ለደረሰው ጉዳት ተከሳሹ ተጠያቂ መሆኑ የተነገረ ሲሆን የዋይት ሀውስ የፀጥታ መዋቅር ላይ ምርመራ እንዲካሄድ የሚጠይቁ ድምፆችም እየተሰሙ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በፕሬዝዳናት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ የክስ የቀረበበት ግለሰብ ጥፋተኝነቱ ከተረጋጋጠ የዕድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቀው የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
