EthiopiaNews

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት ስምምነት

የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍና ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ አጋርነቱን ለማጠናከር መስማማቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የ2026 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ የጸደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን ከአውሮፓ ኅብረት የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጆሴፍ ሲኬላ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት መደረጉ ነው የተገለጸው።

በዚህም የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ይበልጥ ለማሻሻል፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚያስችሉ ስራዎችና ቀጣይነት ባለው የኢኮኖሚ እድገት ግቦች ላይ በትብብር ለመስራት አቅጣጫ መቀመጡም ተጠቁሟል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv