LatestNews

ኢትዮጵያ በ2017 ለዜጎቿ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ እየሰራች መሆኗን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተናግረዋል።

ሚንስትሩ ይህንን የተናገሩት በዌቢናር በተካሄደው የዩይትድ ኪንግደምና የአፍሪካ የኢነርጂ ሚንስተሮች ሲምፖሲየም ላይ ነው፡፡

ሲምፖዚየም ላይ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 አመታት ከ10000 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም እንደሚኖራት ሚንስትሩ የተናገሩ ሲሆን በሚቀጥሉት 10 አመታት ደግሞ ኢትዮጵያ 20 ሺህ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር አቅዳ እየሰራች መሆኗንም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ2025 ኢትዮጵያ በግሪድና በኦፍ ግሪድ ለዜጎች #ሙሉ በሙሉ ሃይል ለማቅረብ ያለመች መሆኑን ጠቁመው ይሁንና ግን ዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ሃገራት ባለሃብቶች በዘርፉ ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሲምፖዚየሙ ላይ የኢትዮጵያ፣ የሞሮኮ፣ የግብጽ፣ የሞዛምቢክና የሞሪታኒያ ሃገራት የኢነርጂ ሚንስትሮች ንግግር ማድረጋቸውን በተጨማሪ 183 ባለድርሻዎችም የዌቢናር ውይይቱን መታደማቸውን ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።