ከሳኡዲ ተመላሽ ዜጎች
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 439 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን አስታወቀ።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 7 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 380 ወንዶች እና 57 ሴቶች እንዲሁም 2 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 49ኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ሚኒስቴሩ ያለፈው መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ67 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
መረጃው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
