የትራፊክ አደጋ
በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ደሃና ወረዳ ከእብና ከተማ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በደሃና ወረዳ ቀበሌ 9 ድግሽዋ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡
በአደጋውም 18 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ 62 ሰዎች ደግሞ ለከባድ እና ቀላል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡
ተጎጂዎች በደሃና ወረዳ አምደወርቅ ጤና ጣቢያ እና በአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
