EthiopiaNews

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሚሆነው የኤሌክትሪክ እና የውኃ ፍጆታ መጠን ታውቋል።

በወር እስከ 200 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እና እስከ 15 ሜትር ኪዩብ የውኃ ፍጆታ የሚጠቀሙ መኖሪያ ቤቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መደረጋቸውን የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ትላንት ነሐሴ 30/2016 ይፋ ያደረገው መመሪያው በቅርቡ ውኃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ የተጣለውን አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ ለማድረግ በህዝብ ዘንድ ሲጠበቅ የነበረ መመሪያ ነው ብሎታል ።