InternationalNews

በአሜሪካ የፍትሕ ሥርዓት ጣልቃ ገብነት?

የዶናልድ ትራምፕ ጠበቆች በአሜሪካ የፍትሕ ሥርዓት ጣልቃ ገብነት እየታየ ነው ሲሉ በፍርድ ቤት ተከራክረዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአራት ወንጀሎች መከሰሳቸው የሚታወስ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንዱና ትናንት ፍርድ ቤት ያየው የምርጫ ውጤትን ለመቀልበስ በመሞከር ነበር የተከሰሱት፡፡
ከወራት በኋላ ጉዳዮች በፍርድ ቤት በጠበቆቻቸው በኩል ቢታይም እርሳቸው ግን በፍርድ ቤት አለመገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ጠበቆቻቸውም ክሱ ዳግም መታየት የጀመረበት ሰዓት ትክክለኛ አይደለም በማለት መከራከራቸውና በፍትህ ስርዓቱም እምነት እንደሌላቸው መናገራቸው ተገልጿል፡፡