የሂውማን ራይትስ ዎች ማሳሰቢያ
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ሂውማን ራይትስ ዎች የሳዑዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመውን የሞት ቅጣት እንዲያቆም አሳስቧል፡፡
ሂውማን ራይትስ ዎች ባወጣው መግለጫ በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የተደቀነውን የሞት ቅጣት በአስቸኳይ ለማስቆም እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገቢው የሕግ አሰራርን ባልተከተለ መንገድ የሞት ፍርድ ቅጣት ተደቅኖባቸዋል ሲል ያስጠነቀቀው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ቢያንስ 65 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ምክንያት የሞት ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይችላል ነው ያለው፡፡
የሳዑዲ ባለሥልጣናት እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሌሎች ሦስት ሰዎችን በስቅላት መቅጣታቸውንም የጠቀሰው ተቋሙ ከታሠሩ አንስቶ በአግባቡ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፤ በቀረቡበት አጋጣሚም አስተርጓሚ እንዳልነበራቸውና የተላለፈባቸውን ፍርድ ምንነት እንዳልተረዱም ጠቅሷል።
እነዚህ ስደተኞች በአስቸጋሪው የስደት መስመር በየመን በኩል ወደ ሳውዲ የገቡ መሆናቸውን ያመለከተው ተቋሙ የኢትዮጵያ መንግስት፣ የሳኡዲ አረቢያ አጋሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጣልቃ እንዲገቡም ጠይቋል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
