የአሜሪካ ኪሳራ
ፔንታጎን አሜሪካ በኢራን ጦርነት እስካሁን ድረስ 25 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ማድረጓን አሳውቋል።
ፔንታጎን ስለኢራን ጦርነት በትላንትናው ዕለት ለሀገሪቱ ኮንግረስ የወታደራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ይህንን ያሳወቀ ሲሆን ይህም ወጭ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የአጋማሽ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
አሜሪካ በኢራን ጦርነት ላይ ያወጣችው 25 ቢሊዮን ዶለር የሀገሪቱ የህዋ ምርምር ጣብያ ወይም ናሳ ዓመታዊ በጀት ጋር እኩል መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡
ሆኖም ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ጦርነት በተጀመረ በ6 ቀናት ውስጥ ብቻ 11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር አሜሪካ ወጪ ማድረጓን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ይህ የፔንታን አሀዝ በጣም አንሷል የሚሉ ወገኖች መኖራቸውንም ጠቅሶ የዘገበው አሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
