InternationalNews

የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ

አሜሪካ የሆርሙዝ ሰርጥ እንዲከፈት የተለያዩ ሀገራትን ያካተተ ዓለምአቀፍ ጥምረት እንዲፈጠር እንደምትፈልግ ተገለፀ።

ሮይተርስ ከአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሻቅብ ያደረገውን የሆርሙዝ ሰርጥን መዘጋት ችግር ለመፍታት ዋሽንግተን የሌሎች ሀገራትን ተሳትፎ ትፈልጋለች፡፡

ይህ በአንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ወደ ድርድር እንድትመለስ በሀገሪቱ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ስለመውሰድ እና አለመውሰድ ለመወሰን በዛሬው ዕለት ዝርዝር መረጃዎች ይቀርብላቸዋል ተብሏል፡፡

የሆርሙዝ ሰርጥ ለረጅም ጊዜ ተዘግቶ መቆየቱን ተከትሎም የዓለም የነዳጅ ዋጋ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በመጨመር የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 126 ዶላር መድረሱም ነው የተመለከተው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv