የህብረት ለምርጫ ትዝብት
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ታዛቢዎች 99 በመቶ ያለምንም ገደብ ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ገብተው መታዘብ መቻላቸው ተገልጿል።
ህብረት ለምርጫ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስከ ቀን 7 ሰዓት ያሉትን የትዝብት ግኝቶችን ብቻ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ያደረገ ሲሆን ለምርጫው 2 ሺህ 258 ተቀማጭ እና 891 ተንቀሳቃሽ በአጠቃላይ 3 ሺህ 149 ታዛቢዎችን ከማለዳው 11:30 ጀምሮ በ2 ሺህ 258 ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ አሰማርቶ እየታዘበ እንደሆነም ገልጿል።
በዚህም እያንዳንዱ ታዛቢ ቢያንስ 6 ጣቢያዎችን እንዲታዘብ መሰማራታቸውንና ታዛቢዎች 99 በመቶ ያለምንም ገደብ ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎቹ ገብተው መታዘብ መቻላቸውንም ጠቅሷል፡፡
ታዛቢዎች ከተሰማሩባቸው 2 ሺህ 258 ጣቢያዎች ውስጥ 2 ሺህ 183 የምርጫ ጣቢያዎች ወይም 97 በመቶ ያህሉ የህብረቱ ታዛቢዎች በስፍራው ሲደርሱ የምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው እንደነበሩ አስረድቷል።
ኅብረቱ ከታዘባቸው 2 ሺህ 258 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች መካከል 42 በመቶ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሂደቱ ከማለዳ 12 ሰዓት በፊት መጀመሩንና 57 በመቶ የሚሆኑ ጣቢያዎች ደግሞ ከማለዳ 12 እስከ 1 ሰዓት ባለው ጊዜ መጀመሩን ታዝቧል።
በተቃራኒው 32 የምርጫ ጣቢያዎች ወይም 1 በመቶ የሚሆኑ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ከጠዋቱ 1 ሰዓት በኋላ መጀመራቸውንና በ3 ጣቢያዎች ይህን መግለጫ እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አልተጀመረም ነው ያለው፡፡
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
