EthiopiaNews

የሊባኖስ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች

በማስ ትራቭል መርሃግብር ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ለሚፈልጉ ዜጎች የምዝገባ ሂደት ዛሬ እና ነገ እንደሚከናወን በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ለምዝገባ ሂደቱ ከሚከፈሉ ክፍያዎች መካከል ለጀነራል ሴኩሪቲ የሚከፈለው የቅጣት ክፍያ ወይም ቀራማ እንዲቀር መደረጉን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ዜጎች በዚህ እድል እንዲጠቀሙም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በመሆኑም ተመዝጋቢዎች የአገልግሎት ክፍያ 110 ዶላር ብቻ እንደሚከፍሉ የተገለጸ ሲሆን የአውሮፕላን ቲኬት ክፍያ በተመለከተ በረራ ሲጀመር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመነጋገር የክፍያ መጠኑን እንደሚያሳውቅ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ጨምሮ አስታውቋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/