የኤሮስፔስ ፋብሪካ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ጋር በመሆን ያስገነባው የአውሮፕላን መለዋወጫዎችን የሚያመርት የኤሮስፔስ ፋብሪካ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚመረቅ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይሄን ያሉት “የሉዓላዊነት ልብ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የበተለይ ቃለመጠይቅ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሚመረቀው የኤሮስፔስ ፋብሪካ የአውሮፕላን መለዋወጫዎችን የሚያመርት መሆኑን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በየጊዜው የአውሮፕላን መለዋወጫዎችን ስትገዛ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን መለዋወጫዎችን እዚሁ እንድታመርት መወሰኑን ነው የተናገሩት።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
