የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት
ኢትዮጵያና ቻይና ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በአጋርነት ለማለፍ በሁሉም መስኮች ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መስማማታችውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን አምባሳደር ሁ ቻንግቹን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ሀገራቱ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ያሉ አገራት የተጋረጠባቸውን ፈተና በመግታትና ዕድሎችን በአግባቡ በመጠቀም በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹ ሲሆን ለዚህም ቻይና ወሳኝ ሚና እንዳላት ጠቁመዋል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
