የሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ስንብት

እጅግ ድንቅ ብቃት ያለው የአርጀንቲናዊው ኮከብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ በርካታ ስኬቶች ከተጎናፀፈበት ባርሴሎና ክለብ ጋር መለያየቱ ለክለቡ ደጋፊዎች እጅግ ከፍተኛ ሃዘን ፈጥሮባቸዋል።የኮከቡ አድናቂዎች እና የክለቡ አፍቃሪያን እጅግ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ሲሆኑ አንድ ደጋፊ ግን በስታዲየም አካባቢ በመገኘት የሜሲን ማልያ በመያዝ ልብ በሚነካ ሁኔታ ተንሰቅስቆ ሲያለቅስ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም አለ።#ለምን ለቀቀ?#በባርሳ እና በሊዮኔል ሜሲ መሃል የተፈጠረውስ ጉዳይ ምንድነው?ፋብሪዚዮ ሮማኖ በይፋዊ ማህበራዊ ድረ-ገጹ ላይ እንደገለጸው ትላንትና ሜሲ ከአባቱ ጋር ሆኖ ኮንትራቱን እስከ መጪው 2026 አራዝሞ ለመፈራረም ባርሴሎናል ተገኝቶ ነበር።ከሳምንታት በፊትም ከሜሲ ጋር ባላቸው ስምምነት ጉዳይ ላይ ቡድኑን እና የገበያ ስትራቴጂያቸውን በተመለከተ ምንም አይነት ችግር አልነበረም።የፊርማ ስነ-ስርአቱን ይፋ ለማድረግም ባርሴሎና ዝግጅት ስያደርግ የነበር ሲሆን በሚፈጸመው ክፍያ ዙሪያ ከላሊጋ ጋር ንግግር ካደረጉ በኋላ ለሜሲ አሁን ስምምነታቸውን ማድረግ እንደማይችሉ አሳውቀውታል።ሜሲም ይህን ተከትሎ ጉዳዩን በግልጽ ማሳወቃቸውን አድንቆ ነገር ግን ጉዳዩ ከባርሳ ገፍቶ መምጣቱ እጅግ አስደንግጦት ነበር።#በቀጣይስ ኮከቡ ማረፊያው የት ይሆን?ትላንት ለሊት ላይ ከፒኤስጂ ዋና አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ጋር በስልክ ከመነጋገር ባለፍ የሚዘዋወርበትን ሂደት የተወያዩ ሲሆን ክለቡም ዝውውሩ እንዲሳካ ውስጣዊ ንግግሮችን በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።የሚደረገውም ዝውውር በከፍተኛ ሂሳብ መሆኑን ተከትሎ ፒኤስጂዎች ዝውውሩ ተፈፃሚ እንዲሆን ከሌሎች የቢዝነስ አጋሮቻቸው ጋር እየተወያዩ መሆኑ ተገልጿል ።