InternationalLatestNews

በቻይና የጎርፍ መጥለቅለቅ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ300 ሲያልፍ በርካቶች አሁንም የደረሱበት አልታወቀም፡፡

በቻይና በቅርቡ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከ300 ሲያልፍ በርካቶች አሁንም የደረሱበት አልታወቀም፡፡እጅግ የከፋው አደጋ የደረሰው የሄናን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በዤንግዙ ከተማ ሲሆን የባቡር ጣቢያዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀው የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሎም ነበር፡፡አሁን ላይ በአደጋው የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከበፊቱ በ3 እጥፍ ጨምሮ 302 ከመድረሱ በተጨማሪ በዤንግዙ ብቻ ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 47 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ አልጀዚራ ዘግቧል።ለሶስት ተከታታይ ቀናት የጣለው ከባድ ዝናብ በአመቱ ከፍተኛው ሆኖ ሲመዘስገብ በዚህም ነዋሪዎች መውጫ አጥተው የከተማይቱ መንገዶችም ተጥለቅልቀውም ነበር።የከተማዋ ነዋሪዎችም በበኩላቸው በዚህ በተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎችም በባቡር ጣቢያ አቅራቢያ አበባ በማስቀመጥ ሀዘናቸውን እየገለጹ እንደሚገኙ አልጀዚራ ዘግቧል

።ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።Telegram: https://t.me/ebstvworldwideFollow us on: https://linktr.ee/ebstelevision