InternationalLatestNews

ሶስተኛዉ የኮቪድ-19 ክትባት እስከ መጪው መስከረም መገባደጃ ድረስ እንዲገታ የዓለም ጤና ድርጅት ጠይቋል።

ሶስተኛዉ የኮቪድ-19 ክትባት እስከ መጪው መስከረም መገባደጃ ድረስ እንዲገታ የዓለም ጤና ድርጅት ጠይቋል።ይህ ሲሆን በሁሉም አገራት 10 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ክትባቱን እንዲያገኝ ይረዳል ሲሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ተናገሩ። ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ለዜጎቻቸው ለመስጠት ማሰባቸውን ካሳወቁ አገራት እስራኤልና ጀርመን ይገኙበታል። ኃላፊው ደሃ የሚባሉት አገራት በክትባት ሂደቱ ወደኋላ እየቀሩ እንደሆነ አሳስበዉ ክትባቶቹ ተመልሰው በመሰብሰብ እና ወደ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት መሰራጨት እንዳለበት ማሳሰባቸዉ ቢቢሲ ዘግቧል።በሌላ በኩል እስራኤል እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ተጨማሪ ክትባት እንዲያገኙ እያሰራጨች ሲሆን ጀርመን ደግሞ ሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶችን 3ተኛ ዙር ለማሰራጨት ማሰቧን አስታውቃለች። እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም ተጋላጭ ናቸው የተባሉት የተለዩ ዜጎች ከመጪው ወር ጀምሮ ማጠናከሪያ ክትባቶችን እንደሚያገኙ ተገልጿል።