EthiopiaLatestNews

ሱዳን 1ሺ ሜጋዋት የኤሌትሪክ ሃይል ለመግዛት ጥያቄ ማቅረቧ ተሰማ::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ሱዳንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት ፍላጎት አሳይተዋል ሲሉ ተናገሩ።ሃይል የመግዛት ፍላጎት ኣሳይተዉ ድርድር በማድረግ ላይ ከሚገኙ ሃገራት መሃከል ደቡብ ሱዳን ኬንያ እና ጅቡቲ ተጠቃሾች ናቸዉ። በቅርቡ ሱዳን 1ሺ ሜጋዋት ሃይል እንደምትፈልግ ማሳወቋን ጠቁመዋል። ባለፈው ወር የተቋሙ ሠራተኞች ወደ ካርቱም አቅንተው የተነጋገሩ ሲሆን የሱዳን ባለሙያዎችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ውይይቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።ለኬንያ የኤሌትሪክ ሃይል አቅርቦት 5መቶ ኪሎ ዋት መሸከም የሚችል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑን አሳዉቀዋል። ኢትዮጵያ ከኬንያ አልፎ ታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ 2ሺ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍ የሚያስችል መሠረተ ልማት መዘርጋቷንም ተናግረዋል።አሁን ሀገራቱ እያሳዩት ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎትም በግድቡ ያላቸውን ተስፋ አመላካች ነዉ ተብሏል።