InternationalLatestNews

ሱዳን የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ላይ የጦር ወንጀል ክስ እንዲከፈትባቸው ፍላጎት እንዳላት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ አስታወቀች፡፡

ሱዳን የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ኦማር አል-በሽር ላይ በዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የጦር ወንጀል ክስ እንዲከፈትባቸው ፍላጎት እንዳላት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ አስታወቀች፡፡

ለአይሲሲ ወይም ለዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በቀድሞ መሪ ላይ የተመሰረተውን ክስ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ካቢኔያቸው ካለምንም ተቃውሞ ድጋፍ መስጠቱን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በ2019 ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ የገጠማቸው ኦማር አል-በሽር በወታደራዊ ኃይል ከስልጣን የተወገዱ ሲሆን በሙስና ወንጀል ተከሰው የሁለት ዓመት እስር ተፈርዶባቸው በእስር ላይ መቆየታቸውም ይታወሳል።

በተጨማሪም በቀድሞው ፕሬዝዳንት አስተዳደር ዘመን ላይ ተጎጂ ለነበሩ ዜጎች ፍትሐዊ ፍርድ ለመስጠት ቃል ገብቶ እንደነበር ሲገልፅ በወቅቱም እስከ 300ሺ የሚደርሱ ዜጎች መገደላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ታዲያ አሁን የሀገሪቱ ካቢኔ ኦማር አል-በሽር በጦር ወንጀል እንዲጠየቁ ድጋፍ ቢሰጥም ውሳኔው በሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊጸድቅ ይገባል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡