EthiopiaLatestNews

አገልግሎት መስጠት ተስኖት የቆየው የጢስ አባይ 2 ኃይል ማመንጫ አንድ ዩኒት በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ::

አገልግሎት መስጠት ተስኖት የቆየው የጢስ አባይ 2 ኃይል ማመንጫ አንድ ዩኒት በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ በደለል መሞላትና ተርባይን ብልሽት ምክንያት ላለፉት 7 ዓመታት ከስራ ውጪ ነበር ተብሏል። የሀይል ማመንጫው ችግሩን ለመፍታትና ወደ ስራ ለማስገባት በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መጠየቁም ተነግሯል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት የጥገና ስራው በተቋሙ ባለሙያዎች አማካኝነት እየተከናወነ እንደሆነ ተሰምቷል። በቅርቡም ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር እስከ 33 ሜጋዋት ኃይል ማመንጨት እንደሚችል ከኤሌክትሪክ ሀይል ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።