InternationalLatestNews

በአፍሪካ በዴልታ የኮሮና ዝርያ የሞቱ ዜጎች ቁጥር 80 በመቶ መጨመሩን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

በአፍሪካ በዴልታ የኮሮና ዝርያ የሞቱ ዜጎች ቁጥር 80 በመቶ መጨመሩን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል። በአፍሪካ በዴልታ የኮሮና ቫይረስ ከ1 ወር በፊት የሞቱ ዜጎች ቁጥር 13 ሺ ሲሆን አሁን ላይ ወደ 25ሺ መጠጋቱን የዓለም የጤና ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በዴልታ የኮሮና ዝርያ አማካኝነት የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል። በአህጉሪቱ በ1 ወር በኮቪድ 19 ለህልፈት ከተዳረጉት ውስጥ 64 ከመቶ በደቡባዊ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆን ቀሪዎቹ 24 ከመቶ ደግሞ በሰሜን አፍሪካ ሀገራት ነው። የጤና ድርጅቱ በቀጣይ 2 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ በመላው አለም በኮሮና የተያዙ ዜጎች ቁጥር ከ2 መቶ ሚሊየን ሊያሻቅብ ይችላል ሲል ግምቱን አስቀምጧል።