InternationalLatestNews

ሕፃናት ላይ ወሲባዊ ብዝበዛ የሚያደርሱ ደንበኞቹን የሚለይ ቴክኖሎጂ ይፋ ለማድረግ ማቀዱን አፕል አስታወቀ።

ሕፃናት ላይ ወሲባዊ ብዝበዛ የሚያደርሱ ደንበኞቹን የሚለይ ቴክኖሎጂ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ላይ ይፋ ለማድረግ ማቀዱን አፕል አስታወቀ። በአይፎን ስልካቸዉን ፎቶ ተነስተዉ ወደ አይክላውድ ከመላካቸው በፊት ቴክኖሎጂው ሕፃናት ላይ ወሲባዊ ብዝበዛ ተፈፅሞ ከሆነ ያጣራል። ቴክኖሎጂው ይህን መሰል ምስል ካገኘ በሰዎች ተጣርቶ ጉዳዩን ለፖሊስ አሳልፎ እንደሚሰጥ አፕል አስታዉቋል። ነገር ግን ይህ ቴክኖሎጂ ነፃነትን ይጋፋል የተባለ ሲሆን መንግሥታት ሕዝባቸው ላይ ለመሰለል ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል ቅሬታ እየቀረበበት መሆኑን ቢቢሲ በዘገባዉ አመላክቷል። ካስም የተባለው ቴክኖሎጂ ጥቃት የደረሰባቸ ልጆች ምስሎቻቸዉን ከማዕከል እና ከሌሎች ድርጅቶች ያገኛቸውን ፎቶዎችን በመጠቀም ወደ ኮድ ይቀይርና በአፕል ምርቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይደረጋል። የመለየት ኃይሉ መቶ በመቶ ነው ያለዉ ኩባንያዉ ከአንድ ትሪሊዬን ፍለጋዎች አንዱን ሊስት እንደሚችል ጠቁሞ አቅም እንዳለዉ ይፋ አድርጓል።