EthiopiaNews

የመንግስት ህንጻዎች በአ.አ

በማእከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ያሉ 6 ሺህ 945 ያህል የመንግስት ህንጻዎችን በዘመናዊው የንብረት መረጃ ሥርዓት መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ገለጸ፡፡

እስካሁን ወደ 700 የሚደርሱ ተቋማት ቋሚ ንብረቶቻቸው ተመዝግበዋል ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አጠቃላይ በተቋማትና በአመራር እንዲሁም በባለሙያዎች ምን ምን ንብረቶች እንዳሉ በትክክል ማወቅ የሚቻልበትና የንብረቶች ወቅታዊ ዋጋም በስርዓቱ መሰረት ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል፡፡

ይሄም በከተማ አስተዳደሩ ስር ያለውን ሃብት በትክክል ቆጥሮ ለማወቅ እንዳስቻለና ለፖሊሲና ህግ አውጭዎች እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩን እየመሩ ላሉ አካላት የተሟላ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት አመቺ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/