የኢትዮ_ዱባይ የንግድ ልውውጥ
በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በአውሮፓውያኑ በ2025 ብቻ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ።
ይህ የተገለጸው የዱባይ የንግድ ምክር ቤት በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የዱባይ – ኢትዮጵያ ቢዝነስ ትብብር ፎረም ላይ ሲሆን በመድረኩም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከ1 ሺህ 660 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በንግድ፣ ሪልስቴት፣ ሎጂስቲክስና መሰል ዘርፎች ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገልጿል።
እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በግብርናና መሰል መስኮች ትብብራቸው እያደገ መምጣቱ የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ ለስራ ብቁ የሆነ የሰው ሀይል ያላት ሃገር በመሆኗ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሃብቶች በሃገሪቱ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
https://ebstv.tv/
