የምርጫ ቅስቀሳ ጊዜን ተከትሎ በጥሞና ጊዜው ሚዲያዎች ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡

የምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ ተከትሎ በጥሞና ጊዜው የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል፡፡ በነዚህ ጊዜያት የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከምርጫ ጋር በተያያዘ ማሰራጨት የሚችሉት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ሀላፊነት ሲኖርባቸው መሆኑን የጠቀሰው ቦርዱ ከዚህ ውጪ ተቋማቱ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትን እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም ብሏል፡፡ከዚህ በሻገር መገናኛ ብዙሃኑ የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት እንደማይፈቀድላቸውም ጨምሮ ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው 4 ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይፈቀድላቸው ስለመሆኑ አዝገንዝቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አክሎም የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ ቦርዱ ጠይቋል፡፡በዚህም መሰረት መገናኛ ብዙሃኑም ሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሚያወጣቸውን መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል ሲል ያሳሰበው ቦርዱ የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ሂደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ መሆኑንና በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት መመሪያ መሠረት የጥሞና ወቅት የሚባሉት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት 4 ቀናት መሆናቸውን በማህበራዊ የትስስር ገጹ አሳስቧል፡፡