EthiopiaNews

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችን እየጎበኘ መሆኑን አስታወቀ፡፡

🔸የኢጋድ ታዛቢ ቡድኑ መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ በአዲስ አበባ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን አከፋፈት እና አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።

🔸የቡድን መሪዋ የመጀመሪያ ምልከታቸውን ያደረጉት በመዲናዋ በምርጫ ክልል 17፣ ወረዳ 3 በሚገኘው የሻላ ፓርክ ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 1 ላይ ሲሆን በዚህም የምርጫ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን፣ የጣቢያውን አከፋፈት ሥነ ሥርዓት እና የድምፅ አሰጣጥ አጀማመርን በቅርበት ታዝበዋል።

🔸ታዛቢ ቡድኑ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የድምፅ አሰጣጥ ሒደት፣ የመራጮችን ተሳትፎ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ምቹነት እንዲሁም አጠቃላይ የጸጥታና የምርጫ ድባቡን በቅርበት መከታተሉን እንደሚቀጥልም አሳውቋል፡፡

👉መረጃው ከኢጋድ የተገኘ ነው።

#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews