የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችን እየጎበኘ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የኢጋድ ታዛቢ ቡድኑ መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ በአዲስ አበባ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን አከፋፈት እና አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።
የቡድን መሪዋ የመጀመሪያ ምልከታቸውን ያደረጉት በመዲናዋ በምርጫ ክልል 17፣ ወረዳ 3 በሚገኘው የሻላ ፓርክ ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 1 ላይ ሲሆን በዚህም የምርጫ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን፣ የጣቢያውን አከፋፈት ሥነ ሥርዓት እና የድምፅ አሰጣጥ አጀማመርን በቅርበት ታዝበዋል።
ታዛቢ ቡድኑ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የድምፅ አሰጣጥ ሒደት፣ የመራጮችን ተሳትፎ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ምቹነት እንዲሁም አጠቃላይ የጸጥታና የምርጫ ድባቡን በቅርበት መከታተሉን እንደሚቀጥልም አሳውቋል፡፡
መረጃው ከኢጋድ የተገኘ ነው።
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews
