EthiopiaNews

የሪሜዲያል ፕሮግራም ፈተና

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት 53,620 ተፈታኞች ሀገር አቀፍ የሪሜዲያል ፈተና ዛሬ መውሰድ መጀመራቸውን አስታወቀ።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ ከ 30ሺ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ፣ ከ23 ሺ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 53,620 ተፈታኞች ፈተናውን እየወሰዱ ነው ብሏል።

የሪሜዲያል ፈተናው በ61 የፈተና ማዕከላት በበይነ መረብ እየተሠጠ እንደሚገኝ አገልግሎቱ ገልጿል።

አገልግሎቱ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 4- 12/2018 ዓ/ም የሚሰጥ መሆኑን ገልፆ ሁሉም ተፈታኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። መረጃው ከትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews