ፌዴሬሽኑ ስለ ምርጫው
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ባሳለፍነው ሰኞ በተካሄደው 7ኛ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከ32 ሺህ በላይ ወጣቶችን በታዛቢነት አሳትፎ እንደነበረ አሳውቋል።
ፌዴሬሽኑ ይህንን ያሳወቀው ትላንት በሰጠው መግለጫ ላይ ሲሆን በምርጫው በታዛቢነት ከተሳተፉ ወጣቶች መካከል ከ20 ሺህ በላይ ወንዶችና ከ12 ሺህ በላይ ሴቶች ይገኙበታል ብሏል።
በምርጫው እለት የምርጫ ጣቢያዎች ለመራጮች ምቹ እንዲሆኑ፣ አቅመ ደካሞችና ሽማግሌዎች የሚያርፉባቸው ድንኳኖችንና ወንበሮችን በማዘጋጀት ረገድም የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር ገልጿል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ጨምሮም ወጣቶች በመራጭነትም ሆነ በታዛቢነት የነበራቸው ተሳትፎ በአጠቃላይ ከፍተኛ እንደነበረም ጠቁሟል።
ፌዴሬሽኑ አክሎም ከምርጫ በኋላም በተለይ የምርጫው ውጤት ይፋ በሚሆንበት ወቅት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤቱን በጸጋ እንዲቀበሉና ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ወጣቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጿል።
ዘገባው የፍስሐ ደሳለኝ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
