የሰሞኑ የአሜሪካ ድጋፍ ለኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በዚህ ሳምንት ለተለያዩ ተግባራት የሚውሉ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አድርግዋል፡፡
ኤምባሲው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 300 ሺህ ዶላር የሚያወጣ የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና የተግባቦት የትምህርት ክፍል ላስገነባው የሚዲያና የቴክኖሎጂ የስልጠና ማዕከል የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤምባሲው ድጋፉን ያደረገው የኢትዮጵያና አሜሪካን የ120 ዓመታት ግንኙነት ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ተናግሯል።