የሶማልያ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያ
ሶማልያ የኢትዮጵያ አየርመንገድ በግዛቷ እንዳበር እገዳ ልትጥል መዘጋጀቷን ተናግራለች።
የሶማልያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ያቀረብኩት ቅሬታ እስከ ነገ ነሐሴ 17/ 2016 ዓ.ም መፍትሄ ካልተሰጠው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ሶማልያ ከተሞች የሚያደርጋቸውን ሁሉንም በረራዎች አግዳለሁ ማለቱን ብሉምበርግ ዘግቦታል።
ቅሬታው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ወደ ሶማልያ ከተሞች ሲበር የመዳረሻዎቹን ከተሞች አጭር መግለጫ አለመጠቀሙ ሲሆን አየርመንገዱ የአውሮፕላን ማረፊያዎቹን መለያ ኮድ ብቻ በመጠቀም ይበራል ነው የተባለው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።