InternationalNews

የቀድሞው ኦይል ሊቢያ የአሁኑ ኦኤልኤ ኢነርጂ የቶታል ነዳጅ ማደያዎችን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረመ።

ቀድሞ ኦይል ሊቢያ የሚባለው አሁን ኦ ኤል ኤ ኢነርጂ በመባል የሚታወቀው በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ተሰማርቶ ያለውን የፈረንሳዩ የቶታል ኢነርጂ የነዳጅ ማደያዎችን ለመግዛት ስምምነት መፈራረሙ ተነገረ።

በስምምነቱ መሰረት የሊቢያው የነዳጅ ኩባንያ 120 የቶታል ማደያዎችን ፣ አንድ 13ሺ ኪዩቢክ ሜትር የሚይዝ የነዳጅ ዴፖ እና ሌሎች የድርጅቱ ሀብቶችን የሚረከብ ይሆናል።

የሊቢያው የነዳጅ ኩባንያ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ በገበያ ላይ የነበረውን የቶታል ማደያዎች የገዛው በአፍሪካ ኢንቨስመንቱን ለማስፋፋት በሚል እንደሆነ የዘገበው ዥንዋ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews