InternationalNews

በአሜሪካ ነገና ዓርብ እጅግ አደገኛና የተራዘመ ሙቀት ይከሰታል ተባለ።

ይህ ሙቀት ለአንድ ሳምንት ያህል ሊቆይ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን በእነዚህ ቀናት አሜሪካዊያንን ቀን ቀን ከሚገጥማቸው ከባድ ሙቀት ባሻገር በለሊትም ከባድ ወበቅ ያለው የአየር ሁኔታ እንደሚገጥማቸው ተገልጿል፡፡

በአውሮፓ የተከሰተው ከባድ ሙቀት ለቀናት ቆይቶ የበርካታ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ በኋላ አሁን ላይ ወደ ካናዳና አሜሪካ መሻገሩ የተጠቀሰ ሲሆን አማካይ የሙቀት መጠኑም ከ35 እስከ 46 ድግሪ ሴንቲግሬድ ሊደርስ እንደሚችል ነው የተጠቀሰው፡፡

በአሜሪካ አሁን ላይ 120 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ሙቀት ተጋላጭ ይሆናል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ይህ ከባድ ሙቀት ከሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻዎች አንስቶ እስከ ማዕከላዊ የሀገሪቱ ክፍል ድረስ በርካታ አካባቢዎችን ያዳርሳል ተብሏል፡፡

ይህ ከባድ ሙቀት በቀሪ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews