EthiopiaNewsOthers

የባህዳር ዩንቨርስቲ አለም አቀፍ እውቅና

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በአራት የኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች  ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ ።

ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ባደረገው በእንግሊዘኛው አፅራኦተ ቃል ABET ወይም  (Accredition Board for Engineering and Techndogy ) በተባለው የኢንጂነሪንግ የትምህርት ጥራት ኮሚሽን በኩል መሆኑ ተነግሯል።

ትምህርቶቹም በፈረንጆቹ 2022/23 ዩኒቨርሲቲው ለሚሰጣቸው የኬሚካል፣ ሲቪል፣ ኤሌክትሪካል እና የሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍሎች መሆናቸውን የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለኢቢኤስ አዲስ ነገር በላክው የእውቅና መግለጫ አመልክቷል።