EthiopiaNews

የባሕር ትራንስፖርትና የዲጅታል አገልግሎት

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አዳዲስ የዲጂታል እና የኦንላይን አገልግሎት መስጫ አማራጮችን በቅርቡ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ።

ድርጅቱ የሎጅስቲክስ ደንበኞች በቦታቸው ሆነው በኦንላይን እና በሞባይል መተግበሪያ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችሉ አዳዲስ የዲጂታል ስርዓቶችን ለማስጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል።

የዲጅታል አገልግሎቶቹ ደንበኞች የጭነት ዋጋ መጠየቅ ፣የመርከብ ቦታ ማስያዝ ፣ የቀሪ ክፍያ መረጃ ማግኘት ፣ዲጂታል ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ ያግዛል ተብሏል።መረጃው ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv