EthiopiaNews

የባንኩ እርምጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህገ ወጥ የሃዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታውቋል።

ባንኩ ይሄንን ያስታወቀው በዚህ ተግባር ላይ እየተሳተፉ ያሉ ህገ ወጥ አስተላላፊዎች መገኘታቸውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

ባንኩ በህገ ወጥ የሃዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎች፣ ላኪዎች እና ተቀባዮች ላይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነም ገልጿል።

ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ የሚልኩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ህጋዊ የሃዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎችን ብቻ በመጠቀም ከኪሳራ እና ከህግ ተጠያቂነት እራሳቸውን ሊያድኑ ይገባል ያለው ባንኩ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የሃዋላ ገንዘብ አስተላላፊዎች ዝርዝርንም በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል።

መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews