EthiopiaNews

የተሰራጨው የሀሰት መረጃ

🔸የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ካርድ መረጃ አጣሪ ቡድን በምርጫው ዕለት አሳሳች መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን ገለጸ፡፡

🔸ከእነዚህ የተሳሰቱ መረጃዎች መካከል ‹‹TN Commentaries›› የተባለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ በፌስቡክና በትዊተር አካውንቱ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ታጣቂ ኃይሎች ትራንስፖርት እንዲቋረጥ በማድረግ የምርጫ ጣቢያዎችን ኢላማ አድርገዋል በማለት ያወጣው አንዱ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

🔸ሁለት ታጣቂ ኃይሎች ከምርጫ ጣቢያ ፊት ለፊት የተነሱትን ምስል በማድረግ መረጃው መሰራጨቱን የጠቀሰው ካርድ ባካሄደው የማጣራት ስራ ምስሉ መጀመሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን እና ዛሬ ከሚካሄደው ምርጫ ጋር የማይገናኝ አሳሳች እና ሐሰት መሆኑን አረጋግጫለሁ ነው ያለው፡፡

#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv