የአሜሪካና የኢራን የተኩስ አቁም
አሜሪካና ኢራን በመካከላቸው የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማራዘምና በሆርሙዝ ሰርጥ መተላለፊያ ላይ የተጣለውን ክልከላ ለማንሳት መስማማታቸው እየተነገረ ይገኛል።
ሆኖም ይህንን ስምምነት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገና ያፀድቁታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኢራን መገናኛ ብዙሀን ደግሞ ስምምነቱ ገና አለመጠናቀቁን እየዘገቡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ሮይተርስ ከታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የተኩስ አቁም ስምምነቱ በ60 ቀናት መራዘሙ ሲነገር የሆርሙዝ ሰርጥም ለባህር ትራንስፖርት ዳግም ክፍት ይደረጋል፡፡
ምንም እንኳን እንደኢራን ኒውክለር ፕሮግራም የመሳሰሉ ቀጣይ ድርድር የሚሹ ጉዳዮች ቢቀሩም ይህ ስምምነት በዋሽንግተንና ቴህራን መሪዎች ከፀደቀ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም እንዲጸና ለማድረግ ትልቅ እርምጃ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
